
ጎንደር: መጋቢት 09/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በፍትሕ ሚኒስትሩ ጌዲዬን ጢሞትዮስ (ዶ.ር) የተመራ የፌዴራል መንግሥት የሱፐርቪዥን ቡድን በጎንደር ከተማ ገብቷል።
የሱፐርቪዥን ቡድኑ ከጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሃይ እና ከሌሎች የከተማው ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ጋር በመኾን ነው እየመከረ የሚገኘው፡፡
የሱፐርቪዥን ቡድኑ በቆይታው በከተማው ፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ እና ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም በሌሎች አገልግሎቶች አፈጻጸም ዙሪያ እንደሚመክር የፍትሕ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞትዮስ (ዶ.ር) ገልጸዋል።
ቡድን የተለያዩ የመንግሥት ተቋማትን አፈጻጸሞች ይመለከታል፤ ያጋጠሙ ችግሮችን የጋራ ያደርጋል። በተጨማሪም የፌዴራል መንግሥት ድጋፍ እና እገዛ በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ዙሪያ ይወያያል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!