ማኅበረሰቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች ለመፍታት እየሠራ መኾኑን የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ገለጸ።

21

ደብረ ማርቆስ: መጋቢት 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ማኅበረሰቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች ለመፍታት እየሠራ መኾኑን የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ገልጿል። የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ መንበሩ ዘውዴ ባለፉት ወራት በተፈጠረው የጸጥታ ችግር በከተማዋ ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።

ከማኅበረሰቡ ጋር በተደረገ ተደጋጋሚ ውይይት የተፈጠረውን ችግር ወደ ነበረበት ሰላም መመለስ መቻሉን ለአሚኮ ገልጸዋል። ከንቲባው እንዳሉት ከተማ አሥተዳደሩ ሰላምን ከማረጋገጡ በተጓዳኝ ማኅበረሰቡ የሚያነሳቸውን የመልካም አሥተዳደር እና የልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት አየሠራ ይገኛል።

የመንግሥት ተቋማት በተሟላ መንገድ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙም አስረድተዋል። የልማት ሥራዎችም እየተከናወኑ መኾናቸውን አንስተዋል።

አሁን ላይ የተፈጠረውን ሰላም እና የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ለማስቀጠል ማኅበረሰቡ የሰላም ባለቤት ኾኖ እየሠራ መኾኑን ነው የገለጹት።

ከንቲባ መንበሩ የአማራ ሕዝብ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ ሰላማዊ መንገድን መከተል ይገባልም ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleዘመናዊ የመሬት መረጃ ሥርዓት በደብረ ብርሃን ከተማ እየተሠራ ነው።
Next articleበአማራ ክልል የሚነሱ የሕዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ የክልሉ መንግሥት በቁርጠኝነት እየሠራ መኾኑን ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ አስገነዘቡ።