
ዛሬ የምናመሠግን ዶክተር ካትሪን ሃምሊን ነው 🙏
“አገልግሎቴ እስከ ሞት ድረስ ነው!”
🙏 ጥር 24/1924 (እ.አ.አ) ተወለዱ
🙏 በ1958 (እ.አ.አ) ወደ ኢትዮጵያ መጡ
🙏ሥራቸውን የጀመሩት በልዕልት ጸሐይ ኃይለሥላሴ መታሰቢያ ሆስፒታል ውስጥ ነበር
🙏 በ1974 (እ.አ.አ) የፊስቱላ ማዕከል ሆስፒታል መሠረቱ
🙏 ከ61 ዓመት በላይ ከባለቤታቸው ዶክተር ሬጂናልድ ሃምሊን ጋር አገልግለዋል
🙏 ለኢትዮጵያ ባደረጉት ውለታ የክብር ዜግነት ተሰጥቷቸዋል
🙏 የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ላደረጉት አስተዋጽኦ ዕውቅና ሰጥቷቸዋል
🙏 መጋቢት 12/2012 ዓ.ም በ96 ዓመታቸው ሕይወታቸው አልፏል
🙏 የማሕጸን ሀኪም የሆኑት ዶክተር ካትሪን ሃምሊን በኢትዮጵያ በሺህዎች ለሚቆጠሩ በፊስቱላ የተጠቁ ሴቶችን ከሥነ ልቦናዊ እና አካላዊ ቁስለት ለማዳን ችለዋል።
🙏ዶክተር ካትሪን ሃምሊን እናመሠግናለን!
