
አዲስ አበባ: መጋቢት 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ውይይቱ በክልሉ የሚነሱ የሕዝብ ጥያቄዎችን በመለየት የጋራ መግባባት ላይ መድረስ እና የምክር ቤት አባላቱ የሕዝብ ውክልና ኃላፊነታቸውን መወጣት ላይ ያተኮረ ነው።
በመድረኩ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ “ክልሉ ያለበትን ሁኔታ ተረድተን ውክልናችንን በኃላፊነት ልንወጣ ይገባል” ብለዋል።
እንደ ሕዝብ ተወካይ መሥራት ያሉብንን ጉዳዮች ከመለየት ባለፈ የሕዝብ ተጠቃሚነትን ሊያመጡ የሚችሉ ጉዳዮችን ቅድምያ ሰጥተን መሥራት ይኖርብናል ሲሉም አፈ ጉባኤዋ አስገንዝበዋል።
ቅድሚያ ከሚሰጡ ጉዳዮች መካከል የክልሉን ሰላም ዘላቂ ማድረግ ነው ያሉት አፈጉባኤዋ እንደ ፌዴራል መልስ የሚሹ ጉዳዮች የማስመለስ ኃላፊነት መወጣት ይኖርባችኋል ሲሉ የሕዝብ ተወካይ አባላትን ጠይቀዋል።
መድረኩ ከሕዝብ የተሰበሰቡ ጥያቄዎች ቀርበው በክልሉ የተለያዩ ኃላፊዎች እና በርእሰ መሥተዳድሩ ምላሽ ይሰጥባቸዋል።
ዝርዝር መረጃዎችን የምንመለስበት ይሆናል።
ዘጋቢ: በአደራው ምንውዬለት