
ባሕር ዳር: መጋቢት 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የተሾሙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለዋል።
የሹመት ደብዳቤያቸውን ዛሬ ለፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ያቀረቡት የማሊ፣ ህንድ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኬፕቨርዴ፣ ቦትስዋና እና ጃማይካ አዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች ናቸው።
ተሿሚ አምባሳደሮቹ የሹመት ደብዳቤያቸውን ባቀረቡበት ወቅት ከፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!