በከተሞች የሚገነቡ የመሠረተ ልማት ተቋማትን በተቀናጀ መንገድ እንዲከናወኑ ትኩረት መደረጉን አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) ገለጹ።

56

ባሕር ዳር: መጋቢት 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በተቋማት መካከል የሚታየውን ቅንጅታዊ የአሠራር ችግር ለመፍታት እና የተቀናጀ ዘመናዊ የከተማ መሬት ይዞታ መረጃ ሥርዓት ለመገንባት የጋራ መግባቢያ ሰነድ የፊርማ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።

በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተሞች ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) እንዳሉት በከተሞች የሚታየውን የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የገቢ አሠባሠብ፣ የኑሮ ውድነት፣ የሥራ እድል ፈጠራ ችግሮች እና ከመሬት ጋር የሚታየውን ሕገ ወጥነት ችግር ለመፍታት የተቋማትን ቅንጅታዊ አሠራር ማሳደግ ያስፈልጋል።

በከተሞች በተናጠል የሚገነቡ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚያጋጥመውን ችግር ለመቅረፍ እና መሬትን በማዘመን ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር፤ በከተማ እና መሠረተ ልማት ክላስተር ሥር የሚገኙ ስምንት ተቋማት ቅንጅታዊ አሠራርን ማጠናከር ዓላማ ተደርጎ እየተሠራ መኾኑን ነው ያነሱት።

ባለፉት ወራት በከተሞች የነበረው የመሬት ምዝገባ ሥራ ዝቅተኛ እንደነበር ያነሱት ዶክተር አሕመዲን ለዚህም የተቋማት ተናጠላዊ የተለመደ አሠራር አንዱ ምክንያት መኾኑን አንስተዋል። በቀጣይ ወራት በስምንቱ ሜትሮ ፖሊታንት ከተሞች መሬትን የማዘመን ሥራውን ለማጠናቀቅ ትኩረት ይደረጋል ብለዋል። ለዚህ ደግሞ ስምንቱ የክላስተር ተቋማት የጋራ መግባቢያ ሰነድ የፊርማ ሥነ ሥርዓት አካሂደዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ከፌዴራል የሱፐርቪዥን ቡድን አባላት ጋር ተወያዩ፡፡
Next articleበትግራይ ክልል ሰላም እና ልማትን ለማምጣት መንግሥት ቁርጠኛ መኾኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ገለጹ፡፡