“ሕግ የማስከበር ኀላፊነት የወደቀው በአሥተዳደር ጉዳዮች ዘርፍ ተቋማት ትከሻ በመኾኑ ክፍተቶችን ለይቶ መሙላት እና ማስተካከልን ይጠይቃል” አቶ ደሳለኝ ጣሰው

45

ባሕር ዳር: መጋቢት 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአሥተዳደር ጉዳዮች ዘርፍ ተቋማት ያለፉትን ሰባት ወራት እቅድ አፈጻጸም እየገመገመ ነው። በግምገማው የዘርፉ ቢሮዎች የኾኑት ሰላም እና ጸጥታ፣ ሚሊሻ፣ ፖሊስ፣ ፍትሕ፣ ርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት፣ ሲቪል ሰርቪስ፣ ፀረ ሙስና ኮሚሽን እና በክልሉ በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት የሥራ ኀላፊዎች ተሳታፊዎች ናቸው።

ክልሉ ላለፉት ሰባት ወራት የቆየበትን ውስብስብ ቀውስ ተከትሎ ጥልቅ ግምገማ እና ፈጣን የመፍትሔ አቅጣጫዎችን መከተል እንደሚያስፈልግ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማእረግ የአሥተዳደር ጉዳዮች አስተባባሪ እና የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው ተናግረዋል።

በክልሉ የተፈጠረው ቀውስ ዘርፉ የተጣለበትን ኀላፊነት በአግባቡ ባለመወጣቱ የመጣ ነው ያሉት አቶ ደሳለኝ ጣሰው የመልካም አሥተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጡ ቅሬታ የፈጠረ ነበር ብለዋል።

በክልሉ ከተፈጠረው የጸጥታ ችግር በኋላ በዚህ መልክ በየደረጃው የሚገኘውን ባለድርሻ ለመሠብሠብ እድል ሲገኝ ይህ የመጀመሪያው እንደኾነም ነው ያስገነዘቡት፡፡ አቶ ደሳለኝ “ሕግ የማስከበር ኀላፊነት የወደቀው በዚህ ዘርፍ ትከሻ በመኾኑ ክፍተቶችን ለይቶ መሙላት እና ማስተካከልን ይጠይቃል” ብለዋል። ችግሮችን በግልጽ መለየት፣ ምክንያቶቻቸውን መመርመር እና በየተቋሙ ፈጣን የመፍትሔ አቅጣጫ መጠቀም ያስፈልጋልም ነው ያሉት።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየቅጥር የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለአሚኮ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ በቁጥር የሠ/ቅ.ማ/406 /2016 በቀን 20/02/2016 ዓ/ም ባወጣው ሶማሊኛ ሪፖርተር 1 /ደረጃ VIII ቅጥር፣ አፋርኛ ሪፖርተር 1 /ደረጃ VIII ፣ አረብኛ ሪፖርተር 1 /በደረጃ IX ታሳቢ ቅጥር የቅጥር ማስታወቂያ ላይ መስፈርቱን አሟልታችሁ የተመዘገባችሁ ማለትም፡-
Next articleከ2 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶች በከተማ ግብርና የጓሮ አትክልት እንዲያለሙ ለማድረግ እየሠራ መኾኑን የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ አስታወቀ።