
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ጉባዔው የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።
የፍትሕ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ የምክር ቤት አባሉን ያለመከሰስ መብት መነሳት አስመልክቶ ለሕዝብ ተወካዮች ማብራሪያ አቅርበዋል።
በማብራሪያቸውም፤ አቶ ክርስቲያን በአማራ ክልል ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ ከሚንቀሳቀሱ አካላት ጋር አብረው ሲሠሩ እንደነበር የፌዴራል ፖሊስ መርምሮ ለአቃቢ ሕግ ልኳል ብለዋል።
ምክር ቤቱም በውሳኔ ቁጥር 9/16 የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።