
ባሕር ዳር: መጋቢት 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ዛሬ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶችን ለሚጋፈጡ ሴቶች መደገፊያ እንዲሆን የተቋቋመውን ‘ለነገዋ’ ማዕከልን መርቀው ከፍተዋል።
ከሥነልቡና ድጋፍ እና የጤና ክብካቤ ጀምሮ ሙያዊ ሥልጠናዎችን የሚሰጠው ማዕከል አዳዲስ የሥራ ስምሪት መንገዶችን የሚፈጥር እና ሴቶች በማኅበረስቡ ውስጥ ለሚገባቸው ተገቢ ስፍራ ብቁ የሚያደርግ መኾኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!