
አዲስ አበባ: መጋቢት 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የመደመር ትውልድ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) 3ኛ መጽሐፍ ነው። በድምጽ የተተረከው ይህ መጽሐፍ የምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የተካሄደው በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ነው።
መጽሐፉ አምስት ትውልድን ያካተተ እና በ274 ገጾች የተሰነደ ነው። መጽሐፉ በአዲስ ዋልታ በድምጽ ተተርኮም ለሕዝብ ቀርቧል። የምረቃ ሥነ ሥርዓቱ በዓድዋ መታሰቢያ ሙዚዬም የተከናወነ ሲኾን በዝግጅቱ ወጣቱን ትውልድ በመወከል የተገኙት አቶ ዮሀንስ ቢኒያም “የመጽሐፉን ትረካ በአግባቡ ተረድተን በተግባር ልንኖረው ይገባል” ብለዋል።
ወጣቶች የማንበብ ባሕልን ማዳበር እና ራሳቸውን በዕውቀት ሊያበቁ እንደሚገባ አቶ ዮሃንስ መልእክት አስተላልፈዋል። በመርሐ ግብሩ ላይ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡- ራሄል ደምሰው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!