ሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በተመድ ጥላ ስር የሚሰማራ የሰላም አስከባሪ አስመረቀ።

98

ባሕር ዳር: መጋቢት 5/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥላ ሰር የሚሰማራ ሰላም አሰከባሪ የሰራዊት አባላትን እያሰመረቀ ነው።

የእለቱ የክብር እንግዳ የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ኀላፊ ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማን ጨምሮ የመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል ኀላፊ ሜጄር ጀኔራል አዳምነህ መንግስቴ፣ ጀኔራል መኮንኖች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የሚመረቁት 18ኛ እና 19ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አሰከባሪ ሻለቆች ሲኮኑ በደቡብ ሱዳን ጁባ ግዛት የሚሰማሩ መኾናቸውም ተገልጿል ሲል የዘገበው መከላከያ ሚኒስትር ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየዜጎችን የፍትሕ ጥያቄ ለመመለስ የሕግ እና ፍትሕ ማሻሻያዎችን ለመተግበር እየሠሩ መኾኑን የፍትሕ ቢሮ ኃላፊዎች አሳወቁ።
Next articleየጎጃም ኮማንድፖስት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተሰጡትን ተልዕኮዎች በአግባቡ በመወጣት የአማራን ክልል ሰላም ማሻሻሉን ሜጀር ጀኔራል ግዛው ኡማ አስታወቁ።