በምርት ዘመኑ ከ9 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማዘጋጀት እየተሠራ መኾኑን የሰሜን ሽዋ ዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

30

ደብረብርሃን: መጋቢት 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ሽዋ ዞኑ ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ባለሙያ ሁሉምታዬ ዘነበ በዚህ የምርት ዘመን ከ9 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማዘጋጀት እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል።

እስካሁን ድረስም ከ6 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ ማዳበሪያ መዘጋጀቱንም ተናግረዋል። የተፈጥሮ ማዳበሪያን ሁሉም አርሶ አደሮች አዘጋጅተው ቢጠቀሙ መልካም መኾኑን አስረድተዋል፡፡

ከተዘጋጀው የተፈጥሮ ማዳበርያ 1 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የሚኾነው ከ40 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ መበተኑን መምሪያው አስታውቋል።የተፈጥሮ ማዳበሪያ በዘላቂነት የአፈር ለምነትን በመጨመር እና አሲዳማነትን በመከላከል ረገድ ያለው ሚና የላቀ በመኾኑ አርሶ አደሩ ከግብርና ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት ሰፊ ሥራ ሊሠራ እንደሚገባም መምሪያው አስገንዝቧል።

ዘጋቢ፡- ፋንታነሽ መሐመድ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበረመዷን ወር ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ድጋፍ ለማሠባሠብ ዝግጅት መጠናቀቁን የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ገለጸ።
Next articleየዜጎችን የፍትሕ ጥያቄ ለመመለስ የሕግ እና ፍትሕ ማሻሻያዎችን ለመተግበር እየሠሩ መኾኑን የፍትሕ ቢሮ ኃላፊዎች አሳወቁ።