
ባሕር ዳር: መጋቢት 4/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሰሞኑ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች እና ከተለያዩ ክልሎች ተወካዮች ጋር ውይይቶችን አካሂደዋል።
ዛሬም ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ከመጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባቶች ጋር መወያየታቸውን በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው “የሃይማኖት አባቶች በማኅበረሰብ ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ” ብለዋል።
ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር የምናደርጋቸውን ውይይቶች በመቀጠል ዛሬ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ተጉዘው በስብሰባው የተገኙትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባቶችን ተቀብለን ተወያይተናልም ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!