
ባሕርዳር: መጋቢት 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ለቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሠራተኞች እና አመራሮች በአመራርነት ዘመናቸው ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽኦ የምስጋና እና የክብር ሽኝት አድርገውላቸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ ባደረጉት ንግግር የክቡር አቶ ደመቀ መኮንን የካበተ የአመራርነት ልምድ ከተቋም ባለፈ በሀገርም ደረጃ ወደፊትም ተሞክሮ የሚወሰድበት ነው ብለዋል።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ጊዜያቸው በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የጀመሯቸውን መልካም ሥራዎች ተጠናክረው እንደቀጥሉም ተናግረዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!