የአፈር ማዳበሪያን ከጅቡቲ ወደብ ከክረምት በፊት ለአርሶ አደሩ ለማድረስ ጥረት እየተደረገ መኾኑ ተገለጸ፡፡

29

ባሕር ዳር: መጋቢት 4/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በ2016/17 የምርት ዘመን 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ኢትዮጵያ በማጓጓዝ ከክረምት በፊት ለአርሶ አደሩ ለማድረስ እየተሠራ መኾኑ ተገለጸ፡፡

በብሔራዊ የአፈር ማዳበሪያ ቴክኒካል ኮሚቴ ሥር የጂቡቲ የአፈር ማዳበሪያ ኦፕሬሽን ንዑስ ኮሚቴም ጂቡቲ ወደብ ያለውን የሥራ ሂደት እየተከታተለ መኾኑ ተጠቅሷል፡፡
ከፈረንጆቹ ሕዳር 3/2023 ጀምሮ እስከ አሁን ከ939 ሺህ 560 በላይ ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ ጂቡቲ መድረሱም ተገልጿል፡፡

ከዚህ ውስጥ 905 ሺህ 525 ነጥብ 37 ሜትሪክ ቶኑ ወደ ኢትዮጵያ መጓጓዙ እና ቀሪውን የማጓጓዝ ሥራም ተጠናክሮ መቀጠሉን በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

ወደ ሀገር ውስጥ በማጓጓዝ ሥራው ላይ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ሥራው እንዲሳለጥ እየሠራ መኾኑንም ነው ንዑስ ኮሚቴው ያስታወቀው፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article”የዲፕሎማሲ ሥራን በጥበብ እና በእውቀት ማከናወን ይገባል” የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ
Next articleየአካባቢ ወንጀል ችሎት ብቻ የሚስተናገዱባቸው ፍርድ ቤቶች ሊቋቋሙ ነው፡፡