
ባሕርዳር: መጋቢት 03/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተውጣጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለጎብኝዎቹ ገለጻ አድርገዋል፡፡ ጎብኝዎቹም የዓድዋ ድል መታሰቢያ ታሪኩን፣ ጀግንነቱን እና ጽናቱን በሚመጥን መልኩ ታሪክን ያሸጋገረ፣ ትውልድ የሚማርበት እና በወቅቱ የነበረውን አንድነት በሚገልጽ መልኩ መገንባቱ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!