የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት አጸደቀ።

35

ባሕር ዳር: መጋቢት 03/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ 16 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት አጽድቋል።
6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡

የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ የ16 የፌዴራል ጠቅላይ ዳኞች እጩ ሹመት በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎች ለምክር ቤቱ አቅርበው፤ በአባላቱ ልዩ ልዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተሰጠባቸው በኋላ ሹመቱ ጸድቋል፡፡

ምክር ቤቱ የመንግሥት ግዥና ንብረት አሥተዳደር ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ የቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ እንዲሁም የመገናኛ ብዙኅን ባለሥልጣን የሠራተኞች አሥተዳደር ረቂቅ ሕገ ደንብን በሚመለከት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ኢቢሲ ዘግቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article16ኛው የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ይካሄዳል።
Next articleየዋጋ ግሽበትን ለማረጋጋት መንግሥት የተለያዩ የመፍትሔ እርምጃዎችን እየወሰደነው ተባለ።