16ኛው የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ይካሄዳል።

25

ባሕር ዳር: መጋቢት 03/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ይካሄዳል፡፡ ምክር ቤቱ ጉባኤውን ከጠዋቱ ሶስት ስዓት ጀምሮ እንደሚያካሂድም ተመላክቷል።

በዕለቱም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኞች ሹመትን፣ የፌዴራል የመንግሥት ግዥ እና ንብረት አሥተዳደር ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ የቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ እና የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የሠራተኞች አሥተዳደር ረቂቅ ደንብን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡

ምክር ቤቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ የኢትዮጵያ የሜዳይ፣ ኒሻን እና ሽልማት ረቂቅ አዋጅን እና የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለዝርዝር እይታ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች እንደሚመራም ይጠበቃል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ ምርት በመጀመር ሕዝብን ተጠቃሚ ለማድረግ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Next articleየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት አጸደቀ።