
ባሕር ዳር: መጋቢት 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ መጋቢት 3/2016 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡
መክርቤቱ በውሎው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኞችን ሹመት፣ የፌዴራል የመንግሥት ግዥ እና ንብረት አሥተዳደር ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ የቀረበውን ሪፖርት እና የውሳኔ ሀሳብ እንዲሁም የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የሠራተኞች አሥተዳደር ረቂቅ ደንብን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርት እና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ እንዳለው የኢትዮጵያ የሜዳይ፣ ኒሻን እና ሽልማት ረቂቅ አዋጅን በተጨማሪም የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለዝርዝር እይታ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች እንደሚመራም ይጠበቃል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!