“ረመዷን የኅብረት፣ የአብሮነት እና የእዝነት ወር ነው” የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች

20

ደብረ ብርሃን፡ መጋቢት 2/2016 ዓ.ም (አሚኮ) አሚኮ ያነጋገራቸው በደብረ ብርሃን ከተማ የሚኖሩ ሙስሊሞች 1 ሺህ 445ኛው ዓመተ ሂጅራ የረመዷን ፆምን የሃይማኖቱ አስተምህሮ በሚያዝዘው አግባብ በጎ ተግባርን በማድረግ እንደሚያሳልፉት ተናግረዋል።

አማኞቹ ረመዷን የኅብረት፣ የአብሮነት እና የእዝነት ወር ነው ብለዋል። ቅዱስ ቁርዓን የወረደባት ከወራት ሁሉ የላቀችው የረመዷን ወር ከአምስቱ የእስልምና ማዕዘናት አንዱ የኾነው የረመዷን ፆም የሚከወንባት ቅዱስ ወር ስለመኾኗም አንስተዋል።

መረዳዳት እና መተጋገዝ በስፋት በሚዘወተርበት የረመዷን ፆም በሰደቃ እና በዘካ የተቸገሩትን አቅመ ደካሞችን፣ ህሙማንን፣ ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ልጆችን እንዲኹም በተለያዩ ሰው ሠራሽ እና ተፈጥሯዊ ችግሮች እና የሰላም እጦት ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያዎች የሚገኙ ወገኖችን መድረስ እና መርዳት ይገባልም ብለዋል።

አስተያዬት ሰጪዎቹ ማንኛውም የእስልምና ተከታይ ፆሙን ሲያሳልፍ ስለሀገር ሰላም ዱዓ ማለትም ጸሎት ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

ዘጋቢ፡- ሥነ-ጊዮርጊስ ከበደ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በክልሉ ለተፈጠረው መጠነ ሰፊ ቀውስ ችግሮቹ ከውስጥም ከውጭም የሚመነጩ ናቸው” አቶ ይርጋ ሲሳይ
Next article“ያሳለፍናቸው የፈተና ጊዜያት ምግባራችን እና ተግባራችንን መቅረጽ አለባቸው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ