
ደብረ ብርሃን፡ መጋቢት 1/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መጋቢ ሀዲስ ነቃጥበብ አባቡ በነገዉ እለት የሚጀምረውን የዓብይ ፆምን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቀረንጦስ የፆመዉ ፆም ዲያብሎስን ማሸነፍ እንደሚቻል አና የፆምን ዋጋ ለሰዉ ልጆች የገለጠበት ነዉ ብለዋል።
ለሚቀጥሉት ወራት በሚፆም የዓብይ ፆም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ እና በጎ ተግባራትን በማከናዎን ማሳለፍ እንደሚጠበቅባቸዉ የሃይማኖቱ አስተምህሮ ይነግረናል ነዉ ያሉት።
በተፈጥሮ እና ሠራሽ ምክንያት ለችግር የተዳረጉ ወገኖችን መደገፍ ያስፈልጋል ያሉት መጋቢ ሀዲስ ፈጣሪን በጸሎት በመጠየቅ እና በመማጸን የሀገር ሰላም እንዲጸና መሥራት ተገቢ ነዉ ብለዋል።
ዘጋቢ:- ስነ-ጊዮርጊስ ከበደ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!