
ባሕር ዳር: መጋቢት 1/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሕዝበ ክርስቲያኑ የዓብይ ጻም ወራትን የተቸገሩ ወገኖቹን በማሰብ እና በጎ ምግባራትን በማከናወን ሊያሳልፍ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አሳሰቡ።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ ነገ የሚጀምረውን የዓብይ ፆምን በማስመልከት መልእክት አስተላልፈዋል።
ብፁዕነታቸው ባስተላለፉት መልዕክትም ጾም ኃጢአትን እና ዲያብሎስን እንዴት እንደሚያሸንፍ ጌታችን እኛን ያስተማረበት ነው ሲሉ መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ጻም ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኝ ድልድይ መኾኑን የጠቀሱት ፓትርያርኩ ሕዝበ ክርስቲያኑም በዓብይ ጻም ወራት በጎ ምግባራትን በማከናወን በተግባር ሊተረጉመው ይገባል ብለዋል።
ሕዝበ ክርስቲያኑ ታላቁን የዓብይ ፆም ሲጻም በተለያየ ምክንያት የተቸገሩ ወገኖቹን በማሰብ እና ያለውን በማካፈል ሊኾን እንሚገባም አሳስበዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!