
ባሕር ዳር: የካቲት 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የጤና ሚኒስቴር ከአለርት ኮምፕሬሄንሲቭ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀንን በአዲስ አበባ እያከበረ ይገኛል።
“የሴቶችን አቅም በማጎልበት የጤና ልማቱን እናፋጥን” በሚል የሴቶች ቀን እየተከበረ ነው፡፡
በዚህ በዓል ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ “ሴቶች ከተለምዷዊ አሠራሮች መውጣት እና ማነቆዎችን በመስበር የማኅበረሰቡ አቅም መኾን ይኖርባቸዋል” ብለዋል።
“ሴቶች ተደራራቢ ኀላፊነቶች አሉብን” ያሉት ሚኒስትሯ በተግባራት መደራረብ የሚደክም አቅም እንዳይኖር ማድረግ እና አቅም ማጎልበት ላይ መሠራት አለበት ብለዋል።
ዘጋቢ፡- እንዳልካቸው አባቡ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!