የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ከ47 ሚሊዮን ብር በላይ በኾነ ካፒታል የጤና ጣቢያዎችን አገልግሎት እያስፋፋ መኾኑን አስታወቀ።

4

ባሕርዳር: የካቲት 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ በአቅራቢያ የሚገኙ ጤና ጣቢያዎች ምቹ አገልግሎት እንዲሰጡ የግንባታ ሥራዎችን እየሠራ መኾኑን አስታውቋል።

ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ካምፓስ ሀኪም ግዛው ሆስፒታል ጋር በመተባበር የእናቶች እና ሕጻናት የህክምና አገልግሎትን ለማሳለጥ እየተሠራ ስለመኾኑ የመምሪያው ኀላፊው በቀለ ገብሬ ተናግረዋል።

በተለይ ደግሞ በምጥ መውለድ የማይችሉ እናቶችን በጤና ጣቢያዎች በቀድ ህክምና ማዋለድ በመቻሉ የእናቶችን እንግልት እና በሆስፒታሎች የሚኖረውን መጨናነቅ ማስቀረት መቻሉን መምሪያ ኀላፊው ገልጸዋል።

ከከተማው ውጭ የሚገኙ የጤና ጣቢያዎችን አገልግሎት ለማስፋት ከተማ አሥተዳደሩ 47 ሚሊዮን ብር በመመደብ እየተሠራ መኾኑንም ኀላፊው አስረድተዋል ።

ዘጋቢ፡- ስንታየሁ ሀይሉ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢትዮጵያ እና ዴንማርክ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮችን ያካተተ ምክክር አካሄዱ።
Next articleከ8 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የባቡር ሀዲድ ብረት የዘረፋ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከሚሴ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።