
ባሕር ዳር: የካቲት 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮችን ያካተተ ምክክር ከዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ማካሄዳቸውን ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ.ር) ከዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላርስ ራስሙሴን ጋር ተወያይተዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ከዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላርስ ራስሙሴን ጋር ገንቢ ውይይት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁለቱ ሀገሮች ለቀጣይ ትብብር ጠንካራ መሠረት የሚኾኑ የረጅም ጊዜ ግንኙነቶች እንዳላቸውም ጠቅሰዋል። ውይይቱም በርካታ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮችን ያካተተ እንደነበርም ገልጸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!