
ባሕር ዳር: የካቲት 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ለኢትዮ ፌሪስ ጣና የሀገር ውስጥ የውኃ ትራንስፖርት እንዲያገለግሉ የተገዙት ሁለት ዘመናዊ ጀልባዎች ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ ነው፡፡
ጣና ነሽ ፪ የተሰኘችው ዘመናዊ የሕዝብ ትራንስፖርት ጀልባ እና ሌላኛዋ መለስተኛ ፈጣን ቃኝ ጀልባ በአሶሳ መርከብ ላይ ተጭነው ነው ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ ያሉት፡፡
መጋቢት 24/2016 ዓ.ም ጅቡቲ ወደብ እንደሚደርሱ ይጠበቃል መባሉን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መረጃ አመላክቷል፡፡
ጣናነሽ ዘመናዊ የሰው ማጓጓዣ እና የመዝናኛ ጀልባ ስትሆን 38 ሜትር እርዝመት እና 188 ሰዎችን የመጫን አቅም እንዳላት ተገልጿል፡፡ ለጣና የውኃ ላይ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት እንደምትሰጥ ተመላክቷል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
