
ባሕር ዳር: የካቲት 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የአፍሪካ ልማት ባንክ በኢትዮጵያ በሚያካሂዳቸው ፕሮጀክቶች ላይ ከዶክተር አብዱል ካማራ ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል። ዶክተር አኪንዉሚ አዴሲና የኦባፌሚ አዎሎው የአመራር ሽልማትን በማግኘቱ እንኳን ደስ ያለህ መልዕክትም አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ያላት አጋርነት ውጤታማ ሆኖ ቀጥሏል” ሲሉም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!