
ባሕር ዳር: የካቲት 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ ከአዲስ አበባ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገናል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው “መዲናችን ከከተማ መስፋፋት ጋር የሚመጣ ፍላጎትን የሚያጎሉ ወሳኝ የኾኑ የእድገት እና የለውጥ ሂደት ውስጥ ትገኛለች” ብለዋል።
የዛሬው ዓይነት ስብሰባዎች በሚታዩ ክፍተቶች የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ ብሎም መልካም አጋጣሚዎችን ለመለየት እጅግ አስፈላጊ እንደኾነም አንስተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!