
ባሕርዳር: የካቲት 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ለሚኖሩ ሥደተኞች ብሔራዊ መታወቂያ መሥጠት መጀመሩን የሥደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት አስታውቋል፡፡
ከተለያዩ ሀገራት የመጡ የውጭ ሀገር ዜጎችን በጥገኝነት የምታኖረው ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ለሥደተኞቹ ብሔራዊ መታወቂያ መስጠት ጀምራለች።
የሥደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ጦይባ ሀሰን ይህ ተግባር ዲፕሎማሲያችን ሰው ተኮር እና ለጎረቤት ሕዝብ ጭምር ዋጋ የሚሰጥ መኾኑን በግልጽ የሚያሳይ ነው ብለዋል።
በጉለሌ ሥደተኞች የተጀመረው መታወቂያ የመስጠት መርሐ ግብር ለሥደተኞች የተፈቀደ ተግባራትን ሁሉ ለመከወን ወሳኝ ይኾንላቸዋል ተብሏል።እስካሁን የባንክ አገልግሎት ለማግኘት፣ ሲም ካርድ ለማውጣት እና መሰል ተግባራትን ለመከወን ችግር እንደነበር ያነሱት ሥደተኞችም አኹን ላይ ይህ መታወቂያ እነዚህን እና መሰል ችግሮች ይቀርፍልናል ብለዋል።
ዘጋቢ፡- እንዳካቸው እባቡ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!