የኢትዮጵያን የሳይበር ደኅንነት እና ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ ዲጅታል ሽግግርን መተግበር እንደሚያስፈልግ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር ገለጸ፡፡

32

አዲስ አበባ: የካቲት 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር የሳይበር ደኅንነት እና የዲጂታል ሽግግር ጉባኤ በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው። ጉባኤውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር ከኢትዮጵያ ሳይበር ደኅንነት ማኅበር ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጀው።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ የኢትዮጵያን የሳይበር ደኅንነት እና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ዲጅታል ሽግግርን መተግበር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ዳይሬክተሯ የጉባኤው ዋና ዓላማ በመንግሥት እና በግል ተቋማት የሳይበር ደኅንነትን ማስጠበቅ እና የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከምሁራን ጋር ምክክር ለማድረግ እንደኾነ ተናግረዋል። ጉባኤው ለሁለት ቀናት እንደሚካሄድ በመድረኩ ተገልጿል::

ዘጋቢ፡- ቤቴል መኮንን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 በጀት ዓመት ሁለተኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ ተጀምሯል።
Next articleየምሥራቅ ኢትዮጵያ ታላቁ ጀብዱ-ካራማራ