
ከሚሴ፡ የካቲት 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ከኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሁሉም አካባቢዎች ከተውጣጡ የማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው።
ክልሉን ለማፍረስ የሴራ ተግባራቸውን እየፈፀሙ ያሉ የጥፋት ሀይሎችን ለመከላከል በተሠራው ሥራ በርካታ አካባቢዎችን ወደ አንፃራዊ ሰላም መመለስ ተችሏል ብለዋል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ።
ሕዝባችን እየገጠመው ካሉ ተግዳሮቶች የኢኮኖሚ ልማትና የማኅበራዊ ልማት ስብራቶች እንዳሉበት በመግለፅ በተለይ የወጣቶች የሥራ እድል ፈጠራ ላይ በትኩረት መሥራት ይጠይቃል ብለዋል።
በውይይቱ የሰላም፣ የልማትና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎችን ለርእሰ መሥተዳደሩ እየቀረቡ ይገኛሉ።በመጨረሻም ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።
በውይይት መድረኩ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ፣ የሰሜን ምስራቅ እዝ አዛዥ ሌተናል ጀነራል አሰፋ ቸኮልን ጨምሮ የክልልና የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፦ ይማም ኢብራሂም
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!