
ባሕር ዳር: የካቲት 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ከኢትዮጵያ ሳይበር ደኅንነት ማኅበር ጋር ያዘጋጁት የሳይበር ደኅንነት እና ዲጂታል ሽግግር ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
ጉባኤው የኢትዮጵያን የሳይበር ደኅንነት እና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ እና ሀገራዊ የሳይበር ሥነ-ምህዳር ማጠናከር ላይ በስፋት እንደሚመከርበት ተጠቁሟል።
ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ጉባኤ የሳይበር ደኅንነት፣ የሳይበር ሕግ እና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ከ12 በላይ ጥናታዊ ፅሑፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ተገልጿል።
ጉባኤው ማኅበረሰቡ ስለሳይበር ደኅንነት ግንዛቤ እንዲኖረው የማድረግ ዓላማ እንዳለውም ተጠቁሟል። በጉባኤው የመክፈቻ መርሐ ግብር ላይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግሥት ሃሚድ፣ የኢትዮጵያ ሳይበር ደኅንነት ማኅበር ፕሬዚዳንት ብርሃኑ በየነ (ዶ.ር) ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የዘርፉ መሪዎች እና ተመራማሪዎች ተገኝተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!