
ባሕር ዳር: የካቲት 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የካራማራ ድል የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት ለማስከበር ዋጋ የተከፈለበት ታላቅ ድል መኾኑን የቀድሞ ጦር ሠራዊት አባላት ገለጹ።
ከዓድዋ ድል ጀምሮ በየዘመናቱ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ክብር እና ሉዓላዊነት የማይደራደሩ መኾናቸውን በተግባር ካረጋገጡባቸው ታሪካዊ ሁነቶች መካከል ካራማራ አንዱ መኾኑንም አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ሠራዊት ክብር እና ጀግንነት እስካሁንም መዝለቁን ገልጸው ከሀገር አልፎ የአፍሪካ የሰላም ዘብ በመኾኑ የሁላችንም ኩራት ነው ብለዋል።የካራማራ ድል ኢትዮጵያውያን ለወራሪ ኃይል መቼም ቢኾን እንደማይንበረከኩ ያረጋገጡበት መኾኑን ነው ለኢዜአ የተናገሩት፡፡
የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጀግኖች ወራሪውን የዚያድ ባሬ ጦር ካራማራ ላይ ድል ያደረጉበት እና የኢትዮጵያ አሸናፊነት የታወጀበት ታሪካዊ ዕለት ዘንድሮ 46ኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!