በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በጠገዴ ወረዳ የሰላም ጥሪውን የተቀበሉ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት ተመለሱ።

32

ጎንደር: የካቲት 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ የመንግሥትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ በርካታ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት ተመልሰዋል። መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ከወረዳ እና ቀበሌ አሥተዳደሮች እና ከፀጥታ አካላት ጋር በጥምረት በመሆን በተከናወነው ሰላምን የማስፈን ሥራ በጠገዴ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት መመለሳቸውን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታዘብ አስማረ ተናግረዋል።

ችግሮች ሲያጋጥሙ ወደ እርስ በርስ ግጭት እና ጦርነት ከማምራት ይልቅ በውይይት የመፍታት ሂደት ከሁሉም በላይ ሊቀድም እንደሚገባ አሥተዳዳሪው ገልጸዋል፡፡ ሌሎች የታጠቁ አካላትም ወደ ሰላማዊ ሕይወት ሊመለሱ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ወደ ሰላማዊ ሕይወት ከተመለሱት ወጣቶች የነበሩበት አካሄድ የጥፋት መንገድ መኾኑን፣ ማኅበረሰቡንም በይበልጥ የሚጎዳ እና ሰላምን የሚያደፈርስ መኾኑን ተረድተው የሠላም ጥሪውን በመቀበል ወደ ሕዝብ ተቀላቅለናል ብለዋል። ይህም መደበኛ ሥራቸውን እንደሚጀምሩ የሚያስችል መኾኑን ገልጸዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ረጅም ዓመት ያስቆጠረ የባሕል እና የቋንቋ ትስስር ያላቸው፣ ወንድማማች ሕዝቦች ናቸው” አቶ አደም ፋራህ
Next articleሴቶች በሰላም ግንባታ ዘርፍ ያላቸውን እምቅ አቅም እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀረበ።