“ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ረጅም ዓመት ያስቆጠረ የባሕል እና የቋንቋ ትስስር ያላቸው፣ ወንድማማች ሕዝቦች ናቸው” አቶ አደም ፋራህ

33

ባሕርዳር: የካቲት 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ረጅም ዓመት ያስቆጠረ የባሕል እና የቋንቋ ትስስር ያላቸው ወንድማማች ሕዝቦች ከመኾናቸው ባሻገር በኢኮኖሚያዊ እና በመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ዝርጋታ የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋናው ጽሐረፈት ቤት ኀላፊ አደም ፋራህ ገለጹ።

የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋናው ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ አደም ፋራህ የተመራው ልዑክ በጂቡቲ የገዢው ፓርቲ 45ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የብልጽግና ፓርቲን ወክለው ለገዢው ፓርቲ እና ለጂቡቲ ሕዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። የብልጽግና ፓርቲ ለጂቡቲ ገዢው ፓርቲ ያለውን አብሮነት እና ወንድማማችነት ለማስቀጠል ያለውን ቁርጠኛ አቋምም ገልጸዋል።

በክብረ በዓሉ ላይ የቻይና፣ የኬንያ እና የሩዋንዳ ልዑካን መገኘታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የተመራ ልዑክ የሎጎ ሐይቅ ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክትን ቅድመ ዝግጅት ጎበኘ።
Next articleበማዕከላዊ ጎንደር ዞን በጠገዴ ወረዳ የሰላም ጥሪውን የተቀበሉ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት ተመለሱ።