የአፍጥር እና የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር ሊካሄድ ነው፡፡

24

ባሕር ዳር: የካቲት 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የረመዳን ወርን በማስመልከት “ኢትዮጵያ ታፍጥር” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ እና በተመረጡ የክልል ከተሞች የአፍጥር እና የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር ሊካሄድ ነው፡፡

የማዕድ ማጋራቱ የሚከናወነው በረመዳን ቀናት ሲኾን በጎዳና ላይ ለሚኖሩ፣ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ፣ በሕክምና እና በማረሚያ ቤት ለሚገኙ እና የአልጋ ቁራኛ ለኾኑ ወገኖች መኾኑም ተጠቅሷል፡፡

በባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር የኪነ ጥበብ ሥነ ጥበብ ፈጠራ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ነፊሳ አልመሃዲ እንዳሉት ከበጎ አድራጎት ተቋማት ጋር በመተባበር ዘይት፣ ዱቄት፣ ሩዝ እና የተለያዩ የንጽሕና መጠበቂያዎችን ለመለገስ ታቅዷል፡፡

ለዚሁ ድጋፍ የሚውለው ገቢም ከለጋሽ ተቋማት እና ግለሰቦች ይሰበሰባል ማለታቸውን ኤፍቢሲ አመላክቷል፡፡በዚህም ከ72 ሚሊዮን በላይ ገቢ በማሰባሰብ ከ90 ሺህ የሚልቁ ወገኖችን ለመድረስ ታስቧል ነው ያሉት፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበኩር ጋዜጣ የካቲት 25/2016 ዓ.ም ዕትም
Next articleበርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የተመራ ልዑክ የሎጎ ሐይቅ ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክትን ቅድመ ዝግጅት ጎበኘ።