
ባሕርዳር: የካቲት 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ ላይ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፈዬ፣
በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተሞች ልማት ዘርፍ አሥተባባሪ እና የከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮ ኀላፊ ማማሩ አያሌው (ዶ.ር)፣ የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት አንዲኹም ሌሎች የፌዴራል እና የቢሮ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጂ ቢሮ ኀላፊ ማማሩ አያሌው (ዶ.ር) ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ ሥርዓቱን የጠበቀ የደረቅ እና የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ወሳኝ ነው ነገር ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ቢሮው ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በክልሉ አራት ከተሞች ላይ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ፕሮጀክት እያስገነባ እንደኾነ ቢሮ ኀላፊው ገልጸዋል።
በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተሞች ልማት ዘርፍ አሥተባባሪ እና የከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) የቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓትን ለማዘመን በተለይ ደግሞ እንደ ደብረ ብርሃን ያሉ የኢንዱስትሪ ከተሞች እንዲህ ዓይነት ፕሮጀክት መገንባቱ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል፡፡
የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት በበኩላቸው 323 ሚሊዮን ብር በጀት የተያዘለት ይህ ፕሮጀክት የማኅበረሰቡ የረጅም ጊዜ ጥያቄ እንደነበረ ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡- በላይ ተስፋ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!