
ደብረብርሃን: የካቲት 24/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሊሃም የምግብ ኮምፕሌክስ ፋብሪካ ዛሬ ተመርቆ ወደ ሥራ መግባቱ ተገልጿል። ፋብሪካው ከዱቄት ምርት በተጨማሪ የፖስታ ምርትም እንደሚያመርት ታውቋል። ፋብሪካው 470 ሚሊዮ ብር ወጭ ተደርጎበት ወደ ሥራ መግባቱ በምረቃ ሥነሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።
ፋብሪካውን የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)፣ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ፣ የክልሉ ምክር ቤት የንግድ፣ ኢንዱስትሪ እና ከተማ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢ በላይ ዘለቀ፣ የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ በላይሁን ይርጋ፣ የደብረብርሃን ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ በድሉ ውብሸት እና ሌሎችም የፌዴራል እና የክልል የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ ፡ – በላይ ተስፋዬ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!