በ125 ሚሊዮን ብር ካፒታል በደብረ ብርሃን ከተማ የተገነባው ቴክስታይል ቴክኖሎጂ ተመረቀ።

37

ደብረ ብርሃን: የካቲት 24/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ብርሃን ከተማ በ125 ሚሊዮን ብር ካፒታል የተገነባው ጂንሹ ኢትዮጵያ ቴክስታይል ቴክኖሎጂ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተመረቋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን፣ በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)፣ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ፣ የክልሉ ምክር ቤት የንግድ፣ ኢንዱስትሪ እና ከተማ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በላይ ዘለቀ፣ የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ በላይሁን ይርጋ፣ የደብረብርሃን ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ በድሉ ውብሸት እና ሌሎችም የፌዴራልና የክልል የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተው ነው የተመረቀው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበደብረ ብርሃን ከተማ በተለያየ የምርት ዓይነቶች የተሰማሩ አራት አምራች ኢንዱስትሪዎች ዛሬ ይመረቃሉ።
Next article“የጣሊያንን ገዢነት ከተቀበለ እንኳን ሰው ምድሯ የተረገመች ትሁን”