“ዓድዋ ለሀገር ቅድሚያ መስጠትን የተማርንበት የድል በዓላችን ነው” መንገሻ አየነ (ዶ.ር )

42

ደሴ: የካቲት 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የወሎ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ወሎ ባሕል እና ቱሪዝም ጋር በመተባበር 128ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል
በወሎ ዩኒቨርሲቲ አክብሯል፡፡ በበዓሉ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው አርበኞች፣ የዩኒቨርሲቲዉ የታሪክ ምሁራን እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በተለያዩ ዝግጅቶች ነው የተከበረው፡፡

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህር ረዳት ፕሮፌሰር አሰፋ ባልቻ “ዓድዋ ኅብረትን በመፍጠር በአንድነት መቆምን እና ለጠላት አለመበገርን ያየንበት ነው” ብለዋል ረዳት ፕሮፌሰር አሰፋ የአድዋ ድል ባይኖር ኖሮ ዛሬ ላይ ቀና ብሎ በኩራት መሄድ ባልተቻለ ነበር ሲሉ የበዓሉን ታላቅነት ገልጸዋል፡፡

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት መንገሻ አየነ (ዶ.ር ) በመክፈቻ ሥነሥርዓቱ ላይ “የዓድዋን ድል ያስመዘገብነው እና የሀገራችንን ሉዓላዊነት አስጠብቀን ማቆየት የቻልነው በዓድዋ ድል በማድረጋችን ነው” ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ዓደዋ ላይ ድል የተደረገው በዘመናዊ መሳርያ አለያም ስንቁ በአግባቡ በተቋጠረለት ሠራዊት ሳይኾን ከውስጥ የነበረን ልዩነት ወደጎን በመተው በአንድነት መቆም ስለተቻለ መኾኑን ጠቅሰዋል፡፡

“ዓድዋ ለሀገር ቅድሚያ መስጠትን የተማርንበት የድል በዓላችን ነው” ብለዋል ፕሬዚዳንቱ ዶክተር መንገሻ አየነ፡፡

ዘጋቢ፡- ፊኒክስ ሀየሎም

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየክልሉን ሰላም በዘላቂነት ለማስጠበቅ መዘጋጀታቸውን የቀድሞ ልዩ ኃይል አባላት ገለጹ።
Next article“ሀገራዊ የምክክር ሂደት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ በጥንቃቄ መመራት አለበት” የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር