
አዲስ አበባ ፡ የካቲት 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ባለሀብቶች በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ከከፍተኛ አመራሮች ጋር የምክክር መድረክ አካሂደዋል።
ክልሉ ባለፉት ሦስት ዓመታት በሰሜኑ ጦርነት እንዲሁም አሁን ባለው ግጭት ከፍተኛ የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ኪሳራ እንዲደርስበት ምክንያት መኾኑን ባለሀብቶቹ አንስተዋል።
የአማራ ክልልን የሰላም መደፍረስ ለመፍታት መንስኤውን ለይቶ ማወቅ እና ለችግሩ መፍትሄ ማምጣት ከአመራሩ የሚጠበቅ መኾኑንም ተናግረዋል።
ከክልሉ ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ መንግሥት ችግሩን ለመፍታት ውይይትን እንዲያስቀድም ጠይቀዋል።
የክልሉ መንግሥት ለሰላም ቅድሚያ መስጠት እንዳለበት ነው ያሳሰቡት፡፡ ከዚህ ቀደም ሲያደርግ እንደነበረው ሁሉ ለሰላም ቁርጠኛ ኾኖ በማኀበረሰቡ ዘንድ የሚተገበሩ ሀገርበቀል የግጭት መፍቻዎችን ተጠቅሞ ሰላምን ማምጣት ይገባዋልም ነው ያሉት።
ዘጋቢ፡- ቤተልሄም ሰለሞን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!