“በኮምቦልቻ ከተማ ዛሬ በተጀመረው የከንቲባ ችሎት 18 ጉዳዮች ታይተው አሥተዳደራዊ ውሳኔ ተሰጥቶባቸዋል” የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ መሐመድአሚን የሱፍ

17

ባሕር ዳር፡ የካቲት 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ መሐመድ አሚን የሱፍ ባለጉዳዮችን እና ፈጻሚ ተቋማትን ፊት ለፊት በማገናኘት ጉዳያቸውን መፍታት የሚያስችለውን የከንቲባ ችሎት በዛሬው ዕለት አስጀመርዋል።

ችሎቱ ተመሳሳይነት ያላቸው ጥያቄዎችን በአንድ ጊዜ በመያዝ ፍትሐዊ እና አሥተዳደራዊ ውሳኔ ለመወሰን እንዲሁም የባለጉዳዮችንም ሆነ የአመራሩን ጊዜ በሚቆጥብ ረገድ ፍይዳው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።

በዛሬው ዕለትም 18 ጉዳዮች ታይተው አሥተዳደራዊ ውሳኔ እና የሥራ መመሪያ እንደተሰጠባቸው ከንቲባው ገልጸዋል። ችሎቱ ዘወትር ሀሙስ በሳምንት 1ቀን እንደሚካሄድና ባለ ጉዳይ የሚበዛባቸው ተቋማት በቦታው ተገኝተው ምላሽ የሚሰጡበት የከንቲባ ችሎት መኾኑን የከተማ አሥተዳደሩ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል። ባለጉዳዮች በችሎቱ መደሰታቸውንና ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሰሜን ሸዋ ዞን መንገድ መምሪያ የ2016 በጀት ዓመት የ3 ድልድዮችን ግንባታ ሊያስጀምር ነው።
Next articleበክልሉ ያጋጠመውን የፀጥታ ችግር ሀገር በቀል የግጭት መፍቻ ሥርዓቶችን ተጠቅሞ መቅረፍ እንደሚገባ የአማራ ክልል ባለሃብቶች ገለጹ።