የሰሜን ሸዋ ዞን መንገድ መምሪያ የ2016 በጀት ዓመት የ3 ድልድዮችን ግንባታ ሊያስጀምር ነው።

22

ደብረ ብርሃን: የካቲት 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ሸዋ ዞን መንገድ መምሪያ የ2016 በጀት ዓመት የ3 ድልድዮችን ግንባታ ሊያስጀምር ነው። የመምሪያው ኀላፊ ሙሐመድ አሕመድ የተያዙ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እና በጥራት እንደሚጠናቀቁ አስታውቀዋል። የድልድዮች መገንባት ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎችን ለማቃለል ያግዛልም ብለዋል።

ድልድዮቹ የሚገነቡት በምንጃር ሸንኮራ፣ አሳግርት እና ሀገረ ማርያም ከሰም ወረዳዎች ነው ተብሏል። በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የኮንክሪት፣ በአሳግርት እና ሀገረ ማርያም ደግሞ የተንጠልጣይ እግረኛ ድልድይ እንደሚገነባ ነዉ የተገለጸዉ። ድልድዮቹ የሚገነቡት ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ነው ።

ዘጋቢ፡- ዮናስ ታደሰ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለአህጉራዊ ምጣኔ ሃብት መሳለጥ እና ለነፃ ንግድ ቀጣና ከፍተኛ ፋይዳ አለው የተባለለት የኢ-ኮሜርስ ማዕከል ወደ አገልግሎት መግባቱ ተገለጸ፡፡
Next article“በኮምቦልቻ ከተማ ዛሬ በተጀመረው የከንቲባ ችሎት 18 ጉዳዮች ታይተው አሥተዳደራዊ ውሳኔ ተሰጥቶባቸዋል” የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ መሐመድአሚን የሱፍ