ኢትዮጵያን በውኃ ሀብቶቿ ተጠቃሚ ማድረግ የሁሉም ኀላፊነት መኾኑን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ጅፋር በድሩ ገለጹ፡፡

18

አዲስ አበባ፡ የካቲት 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “የሁለት ውኃዎች ዐቢይ ስትራቴጂ” የሚል ርእስ የተሠጠው መጽሐፍ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት፣ በዋልታ ሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት እና በአብርሆት ቤተ መጽሐፍ ተዘጋጅቶ ለምረቃ በቅቷል።

መጽሐፉ በስድስት ምዕራፍ ተከፍሎ በዓባይ ተፋሰስ እና በባሕር በር ተጠቃሚነት ላይ ዳሰሳ ያደርጋል። በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የመንግሥት ሥራ ኀላፊዎች እና አጋር አካላት ተገኝተዋል።

የአብርሆት ቤተ መጽሐፍት ዳሬክተር ውባየሁ ማሞ በኢትዮጵያ በተለያዩ የሙያ መስኮች የሠለጠኑ እና የተመራመሩ ምሁራን ስትራቴጂያዊ መጽሐፎችን ቢያዘጋጁ ተተኪው ትውልድ ካለፉት ታሪኮች የተሻለውን መርጦ አንዲማርበት ያስችላል ብለዋል፡፡ ዳይሬክተሩ ለሚከሰቱ ተግዳሮቶች መውጫ መንገድ የሚፈጥርለት እንደሚኾንም ነው ያስገነዘቡት፡፡

“እንደ አብርሆት ያሉ ቤተ መጽሐፍትም ከተባባሪ አካላት ጋር በመኾን ሀገራዊ በኾኑ ጉዳዮች ላይ በመመራመር፣ በመጻፍ እና በማሳተም ተተኪው ትውልድ በቀና ጎዳና አንዲሄድ ማገዝ ይኖርባቸዋል” ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ጅፋር በድሩ ኢትዮጵያ ያልተጠቀመችባቸውን ሃብቶቿን በምርምር በመገንዘብ እና የስትራቴጂ መጽሐፍትን በማዘጋጀት በሃብቶቿ ተጠቃሚ ማድረግ የሁሉም ኀላፊነት መኾኑን ተናግረዋል። መጽሐፉም የውኃ ጠቃሚነትን በመዳሰስ ኢትዮጵያ ባሏት የውኃ ሃብቶች ከፍ የምትልበትን መንገድ የሚያስገነዝብ ነው ብለዋል።

ዘጋቢ፦ራሔል ደምሰው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ ።
Next articleኢትዮጵያና ኬንያ በቀጣናው ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር አስታወቀ።