ከፖላንድ የመጡ የሕክምና ባለሙያዎች በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነጻ የሕክምና አገልግሎት እየሰጡ ነው።

23

ባሕር ዳር: የካቲት 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ከፖላንድ የመጡ የሕክምና ባለሙያዎች በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነጻ የሕክምና አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ከሆስፒታሉ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ባለሙያዎቹ በሆስፒታሉ የበሽታ ምርመራ፣ የኒውሮሎጂ እንዲሁም ከካንሰር ጋር ተያይዞ የሚሰጡ የሕክምና አገልግሎቶችን እየሰጡ እንደሚገኙም ተጠቅሷል።

የሕክምና ባለሙያዎች በሆስፒታሉ በሚኖራቸው ቆይታ ለሆስፒታሉ ባለሙያዎች የልምድ ልውውጥ በማድረግና ሥልጠና በመስጠት ያላቸውን ልምድ እንደሚያካፍሉም ተጠቁሟል።

የሕክምና ባለሙያዎቹ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተጨማሪ በጦር ሀይሎች ሆስፒታል እና ሌሎች ተቋማት አገልግሎት እንደሚሰጡ የጤና ሚኒስቴር ዘገባን ዋቢ አድርጎ ኢዜአ ዘግቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በሀገራችን ሰላም እና ልማት እንዲፋጠን ሴቶች አስተዋጽኦ እናበርክት” አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ
Next articleየዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ ።