
ባሕር ዳር፡ የካቲት 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የዛሬው ትውልድ ከዓድዋ ድል እንዲማር እና የዛሬ ችግሮቻችን በዓድዋ መንፈስ እንዲፈቱ ማስቻል የዛሬው ትውልድ የቤት ሥራ መሆኑን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ገልፀዋል።
ዓድዋ “የኅብረ ብሔራዊነት ድምቀት የአንድነት ውጤት” በሚል መሪ ቃል ዓድዋ ላይ ያተኮረ ልዩ ሴሚናር እያካሄደ ይገኛል። በዓድዋ ድል ዙሪያ ስንመክር በእውቀት እና በታሪክ ላይ የተመሰረተ የትምህርት ሥርዓትን ለመዘርጋት ምቹ ሁኔታዎችን የሚፈጥሩ መሆናቸውም ተገልጿል።
በመድረኩ ላይ የጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ወታደራዊ አማካሪ እና የተኩስ አመራር ኃላፊ ሌተናል ጀኔራል አለምሸት ደግፌ፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ እና የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር አየለ በከሪ ከዓድዋ ጋር የተያያዙ ጥናታዊ መጽሐፎችን እይቀረቡ ይገኛሉ ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!