
አዲስ አበባ፡ የካቲት 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ ከሚገኙ ባለሃብቶች ጋር በክልሉ ሰላም እና ልማት ዙሪያ ምክክር እያካሄዱ ነው።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በክልሉ ባለፉት ስምንት ወራት በነበረው ግጭት ከፍተኛ የሰብዓዊ ጉዳት እና የክልሉ ሕዝብ ሃብት የኾኑ ንብረቶች መውደማቸውን ገልጸዋል።
በዚህም የማኅበረሰቡ የረጅም ዘመናት የማንነት መገለጫ የኾኑ የጋራ ትስስር እሴቶች የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸዋል ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ።
በዛሬው እለት ከባለሃብቶች ጋር የሚካሄደው ምክክር የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ በማስገንዘብ በአማራ ክልል የኢኮኖሚ እድገት ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ ያላቸው ባለሃብቶች ለክልሉ ሰላም መረጋገጥ የበኩላቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ነው ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ በመክፈቻ ንግግራቸው፡፡
ዘጋቢ፡- ቤተልሄም ሰለሞን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!