
ባሕር ዳር፡ የካቲት 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ በፕላንና ልማት ሚኒስቴር ተገኝተው ቀጣዩን የሕዝብና ቤት ቆጠራ በተመለከተ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
በተደረገላቸው ገለጻም፥ ቀጣዩ የሕዝብና ቤት ቆጠራ የሶስት ዓመቱ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ልማት ፕሮግራም አካል መሆኑ ተጠቅሷል።
ለሕዝብና ቤት ቆጠራው የሚከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እንዲሁም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
ውይይቱን ተከትሎም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ የሥራ መመሪያና አቅጣጫ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕላንና ልማት ሚኒስቴርን ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!