“የዓድዋ ድል የሀገር ፍቅርን ለሀገር መስዋዕትነት መኾንን በሚያሳይ መልኩ ይከበራል” የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

17

ባሕር ዳር: የካቲት 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል። ሚኒስትር ደኤታ ሰላማዊት ካሳ በመግለጫቸው ዓድዋ የመላው ኢትዮጵያውያን የጋራ ድል እና የአፍሪካ ተምሳሌት እንደኾነ በማሳየት ይከበራል ብለዋል።

ከጀግኖች አባቶቹ ፅኑ እሴትን የወረሰውን መከላከያ ሠራዊት አኩሪ ድሎች እና መልካም ገጽታን በሚያጎላ መልኩ ይከበራል ብለዋል።

የ128ኛው የዓድዋ ድል በዓል በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ክልሎች፣ በከተማ አሥተዳደሮች፣ በተቋማት እና በመላው ዓለም በሚገኙ ቆንስላዎች እና ኢምባሲዎች እንደሚከበርም አስገንዝበዋል።

በዓሉ በመከላከያም በእዞች እና በኮሮች ይከበራልም ብለዋል። የሀገር ፍቅርን ለሀገር መስዋዕትነት መኾንን በሚያሳይ መልኩ እንደሚከበርም አመላክተዋል።

በበዓሉ ወታደራዊ ትዕይንቶች፣ ኪነጥበባዊ ክዋኔዎች ይከወኑበታል ነው ያሉት ሚኒስትር ደኤታዋ። በዓሉ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ውስጥ እንደሚከበርም ገልጸዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ከአየር ንብረት ለውጥ ቀጥሎ የዓለም ትልቁ ስጋት”የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት።
Next article“ትምህርት ላይ ያለውን ስብራት ለመጠገን እና ኢትዮጵያን ለመገንባት የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል” ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)