“ለወሰን እና የማንነት ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እየተሠራ ነው” የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

85

ባሕር ዳር፡ የካቲት 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ለወሰን እና የማንነት ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ገለጹ።

አፈጉባኤው ይህን ያሉት፤ የፌደሬሽን ምክር ቤት እና የፌደራል ፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ በተፈራረሙበት ወቅት ነው።የስምምነት ሰነዱ ሁለቱ ተቋማት የሀብት ማፈላለግ፣የአቅም ግንባታ እና የምርምር ሥራዎችን በጋራ ለመስራት ያስችላቸዋል ተብሏል።

አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ሁለቱ ተቋማት የደረሱት ስምምነት፤ የወሰን እና የማንነት ጥያቄዎችን በዕውቀት እና በምርምር ለመመለስ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል። በስምምነቱ መሰረት የሚሩ ጥናቶች ሕገ መንግሥቱን የመተርጎም እና ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል ሥራዎችን በቀላሉ ለመፈፀም እንደሚያግዝም ተናግረዋል።

የፌደራል ፍትሕ እና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ደግፌ ቡላ፤ የፌደራል ስርዓቱን ለማጠናከር እና የዳበረ ዴሞክራሲን እውን ለማድረግ በስምምነቱ መሰረቱ ተቋማቱ በጋራ ይሠራሉ ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

የሁለቱ ተቋማት የጋራ ስምምነት የመንግስታት ግንኙነትን ማጠናከር፣በሕገ መንግስታዊነት እና በሕግ የበላይነት ላይ የአቅም ግንባታ በመሥራት በክልል እና በፌደራል ደረጃ ተቀራራቢ የሕግ አተረጓጎም እንዲኖርም ያግዛል ተብሏል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የንግዱ ዓለም ሥነ ምግባር”
Next article“መጻሕፍት በወቅቱ ታትመው ባለመቅረባቸው በትምህርት ጥራት ላይ ሌላ ፈተና ተፈጥሯል” የትምህርት ባለሙያ